የሀገር ውስጥ ዜና

ባንኩ ለባቡል ኽይር የበጎ አድራጎት ድርጅት 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Hailemaryam Tegegn

March 12, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለባቡል ኽይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ያስረከቡት ይህ የገንዘብ ድጋፍ፤ በዚህ የረመዳን ወር ለተቸገሩ ወገኖች የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባቡል ኽይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በቀን ከ4 ሺህ 800 በላይ ሰዎችን እንደሚመግብ ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ ከቀናት በፊት የባንኩ ሠራተኞችና ማኔጅመንት አባላት ለመቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 30 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።