አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን ጉራዳሞሌ ወረዳ ከ298 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚገነባው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
በሥነ-ሥርዓቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ባለብዙ መንደር የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከ32 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግና በ21 ወራት ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።