አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንደሀገር በሴቶች የተነሱ ችግሮች ተቀምረው በየደረጃው መፍትሔ እንዲያገኙ ይሠራል ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለም ፀሐይ ጳውሎስ ገለጹ፡፡
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አከባበር የሚገመገም መድረክ አካሂዷል፡፡
ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት፤ መንግሥት የሴቶችን መብት ለማስጠበቅ፣ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
የሴቶችን የአመራርነትና ውሳኔ ሰጭነት ሚና ለማሳደግ እየተወሰደ ባለው ጠንካራ እርምጃም አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ ነው ማለታቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ሴቶች ላይ የሚሠሩ ባለድርሻ አካላትም የተገኙ ስኬቶችን እንዲያከብሩና ያጋጠሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡