አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንሶ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለፕሬዚዳንቱ አሸኛኘት ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር እና የኮሚሽነሮች ይፋዊ የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።