የሀገር ውስጥ ዜና

የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም እና ልዑካቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ጎበኙ

By Abiy Getahun

March 14, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ጉብኝት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ለልዑኩ አቀባበል አድርገዋል።

ጄኔራል ሙባረክ ሙጋጋ እና ልዑካቸው የአየር ኃይልን የበረራ ትምህርት ቤት እና የአቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከልን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል።

ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ ለሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ስጦታ ያበረከቱ ሲሆን፤ በተመሳሳይ የሩዋንዳው ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ለሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተዋል።