የሀገር ውስጥ ዜና

ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣርና የቁርዓን ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

By ዮሐንስ ደርበው

March 16, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር እና ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት ዛሬ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡

‘ቁርዓን – የዕውቀትና የሰላም ምንጭ’ በሚል መሪ ሐሳብ ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድሩ የማጣሪያ መድረክ በአዲስ አበባ ሲካሄድ ቆይቷል።

ውድድሩ ቁርዓንን በልቦናቸው የተሸከሙ ሃፊዝ ወጣቶችን ለማበረታታትና ቀጣይ ተተኪ ትውልዶችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

በመሆኑም ዋናው ሀገር አቀፍ የቁርዓን ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

በዕለቱም ሕዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት ‘ከኢፍጣር እስከ ቁርዓን’ በሚል መሪ ሐሳብ እንደሚከናወን ተጠቅሷል፡፡