የሀገር ውስጥ ዜና

የተፈጥሮ ሀብት ልማትን መተግበር የብልጽግና ማረጋገጫ አንዱ መንገድ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

By ዮሐንስ ደርበው

March 16, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአካባቢን ጸጋ ለይቶ፣ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃን በንቃት መተግበር የሀገር ብልጽግና ማረጋገጫ አንዱ መንገድ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሀገርን ብልጽግና የማረጋገጥን ርዕይ ወደ ተግባር እየቀየሩ ከሚገኙ የሀገራችን አካባቢዎች የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ አንዱ ነው ብለዋል፡፡

በአካባቢው እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችና የአረንጓዴ አሻራ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው ሲሉ አመልክተዋል።