የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አሻድሊ ሃሰን ከክልሉ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

March 21, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን አዲስ ከተደራጀው የክልሉ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በክልሉ የተጀመረውን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሒደት ለማጠናከር በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ መክረዋል፡፡

በቀጣይ የክልሉ መንግስትና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በጋራ ሊፈፀሙ ስለሚገባቸው ሥራዎች እንዲሁም መረጃዎችን መለዋወጥ የሚያስችል የጋራ መድረክ መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መግባባት ላይ ደርሰዋል።

በውይይቱ የፌዴራል የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የአደረጃጃት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዝአብሔርን ጨምሮ የክልሉ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡