የሀገር ውስጥ ዜና

ከነሃሴ ወር የመጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ የተከለከለ ነው- የትምህርት ሚኒስቴር

By Feven Bishaw

August 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ከነሃሴ ወር የመጨረሻ ሳምንት በፊት ምንም አይነት የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ ማካሄድ የተከለከለ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ወላጆችን እያስገደዱ ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡