አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የቀርጫንሼ ግሩብ የጊቤ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ተቋም በአዳሚ ቱሉ ለሚገኙ 300 ቤተሰብ ማዕድ አጋርቷል፡፡
ተቋማቸው የዱቄት እና ዘይት ድጋፍ ማድረጉን የሕዝብ ግንኙነት እና ማኀበራዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ሙሉጌታ ከበደ ተናግረዋል ።
በተመሳሳይ ተቋሙ በጅማ ዞን ሶኮሩ ወረዳ ለ300 አባወራዎች ለበዓል የሚሆን ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡
ለሁለቱም ድጋፎች 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ለተደረገላቸው ድጋፍ አመሥግነዋል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው