አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለትንሳዔ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ።
ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ እንኳን ለክርስቶስ ትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ይህ ቅዱስ የበዓለ ትንሳዔ ዕለት የደስታ የፍስሀና የመልካምነት ቀን ነው ብለዋል።
በዓሉን በፍቅር፣ በሰላምና በመተሳሰብ እናክብር ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው ሲሉ ገልጸዋል።