የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማትን ሃዘን ገለጸች

By Yonas Getnet

April 21, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማትን ሃዘን ገልጻለች፡፡

ቤተክርስቲያኗ ባወጣችው የሃዘን መግለጫ÷ ፖፕ ፍራንሲስ ዛሬ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውንና በዚህም ቤተክርስቲያኗ የተሰማትን ሃዘን ገልጻለች፡፡