አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈተ ሕይዎት የተሰማቸውን ሐዘን ገልፀዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት፤ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈት ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ፤ ለእምነት፣ ለሰብዓዊነት እና ለዓለም አቀፍ ሰላም ማገልገላቸውን አውስተዋል፡፡
ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ፤ መታሰቢያነቱም ለዘላለም ይሁን፤ ሲሉም ፕሬዚዳንቱ በሐዘን መግለጫ መልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡