ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዶናልድ ትራምፕ እና ዘለንስኪ ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

April 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬን አቻቸው ቮለድሚር ዘለንስኪ ዛሬ በጣሊያን ሮም ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በዛሬው ዕለት በተከናወነው የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀብር ሥነ ሥርዓተ ላይ ታድመዋል፡፡

ከሥነ ሥርዓቱ በኋላ ፍሬያማና ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውንና ከሰዓታት በኋላም ውይይታቸው እንደሚቀጥል የሀገራቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

ሁለቱ መሪዎች ባለፈው የካቲት ወር አጋማሽ በነጩ ቤተ-መንግስት ተገናኝተው በከፍተኛ ንትርክ ያለስምምነት ከተለያዩ ወዲህ በአካል ሲገናኙ የዛሬው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡