አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነጌሌ አርሲ ከተማ የኡታ ዋዩ ሞዴል የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን አስጀምረዋል፡፡
ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚከናወነው የትምህርት ቤቱ ግንባታ በ10 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ገላና ወልደሚካኤል (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
የግንባታው ወጪ በትምህርት ሚኒስቴር የሚሸፈን መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ይህንን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች አራት ሞዴል የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታን እንደሚያከናውን ምክትል ኃላፊው ገልጸዋል።
በግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) እና ሌሎች የክልሉና የፌደራል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በጸሃይ ጉሉማ