ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን በዛሬው ዕለት ተከብሮ ዋለ

By Adimasu Aragawu

May 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን በዓለም ለ136ኛ በኢትዮጵያ ለ50ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ኹነቶች ተከብሮ ውሏል፡፡

ዕለቱ “በአምራች ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ምቹ የሥራ ሁኔታ ለማህበራዊ ፍትህ” በሚል መሪ ሐሳብ መከበሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል፡፡

ሠራተኞች፣ የሠራተኛ ማኅበራትና የክህሎት ሥልጠና ተቋማት ለኢንዱስትሪና ሀገራዊ ሰላም እያበረከቱ ላለው አስተዋጽዖ ዕውቅና መስጠት፣ ለሠራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢና የሥራ ላይ ደኅንነት መፍጠር እንደሚገባም አገልግሎቱ አስገንዝቧል፡፡