የሀገር ውስጥ ዜና

ለዘላቂ ሰላም ሕዝብን ባለቤት ማድረግ ይገባል- ምሁራን

By ዮሐንስ ደርበው

May 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰላምን ለማጽናትና ዘላቂ ለማድረግ የሐይማኖት ተቋማት እና ሕዝቡን ባለቤት ማድረግ እንደሚገባ ምሁራን አስገነዘቡ፡፡

የሐይማኖት ተቋማት ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር በሕዝቦች መካከል ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጽናት የጎላ ሚና እንዳላቸው ምሁራኑ አስረድተዋል፡፡

ከሕዝብ ጋር ተከታታይነት ያለው ውይይት ማድረግ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መቅረፍ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሰላምን ለማጽናትና ዘላቂ ለማድረግ የሐይማኖት ተቋማትና ሕዝቡን ባለቤት ማድረግ እንደሚገባም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደንኅነት መምህር የሆኑት ተመስገን ቶማስ (ዶ/ር) በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በሀገሪቱ የመጣውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሕብረተሰቡና የሐይማኖት ተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ደግሞ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደኅንነት ተመራማሪው ያዕቆብ ጬቃ (ዶ/ር) ናቸው።

በአስጨናቂ ጉዱ