የሀገር ውስጥ ዜና

ለኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓል ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

By Melaku Gedif

May 03, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 116ኛውን የኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓል በልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡

የዚሁ አካል የሆነው ሥነ ሥርዓት ነገ ሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች እንደሚከበር አመልክተዋል፡፡

ለበዓሉ አከባበር ሲባልም በመዲናዋ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይደረጋሉ ነው ያሉት፡፡

በዚህ መሰረትም፦

ከ22 አደባባይ ወደ ወደ ቅዱስ ዑራኤል -መስቀል አደባባይ (22 አደባባይ በተመሣሣይ ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ ላይ )

ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ)

ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)

ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ (መስቀል ፍላዎር አደባባይ ላይ )

ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኤግዚብሽን ውስጥ ለውስጥ ወደ ፊላሚንጎ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ )

ከቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር መብራት ( ቅዱስ ቂርቆስ ወደ ጋዜቦ ላይ )

ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ

ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር መብራት (ሜክሲኮ አደባባይ ላይ)

ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ )

ከጥይት ቤት ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ጥይት ቤት መታጠፊያ ላይ )

ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ ላይ )

ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ) ከንጋቱ 10 ሰዓት ጀምሮ መርሐ ግብሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ኮማንደር ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ፣ ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ፣ ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ፣ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም ለዚሁ ፕሮግራም ሲባል ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በመስመሮቹ ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን አሳስበዋል።

በመላኩ ገድፍ