አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አለን ካይዋ እና አቡበከር ሳኒ የመድንን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሃዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡