የሀገር ውስጥ ዜና

የዘመኑን ዐርበኝነት እውን ለማድረግ ራስን ለመቻል በሚደረጉ የልማት ሥራዎች ዙሪያ-መለስ ትጋት ከኹሉም ዜጎች ይጠበቃል። -የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

By ዮሐንስ ደርበው

May 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት 84ኛውን የዐርበኞች ቀን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው ኢትዮጵያ በየታሪክ እጥፋቱ ነፃነቷን አስጠብቃ በጀግኖች ዐርበኞቿ ደም እና ዐጥንት ተከብራ ኖራለች፤ ለዚህም ለጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ለዚህ ያበቁ ጀግኖቿን በመዘከር ተተኪ ዐርበኞችን ለማፍራት እና ነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ እንዲቀጥል ለማድረግ የፋሽስት ጣሊያን የአምስት ዓመታት ወረራ እና ጭፍጨፋ በውድ ልጆቿ ተጋድሎ የተቋጨበትን ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም መነሻ በማድረግ ቀኑ በድል በዓልነት ይከበራል፡፡ ያ ድል በዱር በገደል፣ ርኃብና ጥም ተቋቁሞ ወራሪ ጠላትን በማሸነፍ የተገኘ ነው፡፡

ሀገር ግን በአንድ ወቅት ድል ብቻ ሉዓላዊነቷ ተከብሮ፣ ዝናዋ ገዝፎ እና በዓለም ናኝቶ አይዘልቅም፡፡ በየዘመኑ ጊዜዉ የሚጠይቀዉን ዘርፈ ብዙ ዐርበኝነት ከዜጎቿ ትጠብቃለች እንጅ፡፡ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በዐዲስ ዓውድ በቀጠለ ተጋድሎ ዐርበኞችን እያፈራች ድሎችንም እያስመዘገበች ትገኛለች፡፡ ጨለማን ተጋፍጠዉ የሕዳሴ ግድብን እውን ያደረጉ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ ከዓለም ሕዝብ አምስት እጥፍ ችግኝ ተክለው የሚንከባከቡ፤ በየተሰማሩበት መስክ ከሚጠበቅባቸዉ በላይ ስኬት በማስመዝገብ የምግብ ሉዓላዊነትንና የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ፣ የከተሞቿን ገጽታ እና ዘመናዊነት የሚያሻሽሉ፣ … ዐርበኞች በዘመናችን እያፈራች ትገኛለች፡፡

ቀደምቶቻችን በደምና ዐጥንት የተከሉት ዐርበኝነት በዚህ ዘመን በላብ እና በዕውቀት ወደላቀ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው፡፡ የግዛት አንድነትንና ሉዓላዊነትን በመጠበቅ ረገድ ዛሬም እንደትናንቱ ኢትዮጵያ ጀግኖች አሏት፤ በምድር፣ በአየር፣ በባሕር እና በሳይበር ግንባሮች 24 ሰዓታት በንቃት ኢትዮጵያን የሚጠብቁ ኢትዮጵያውን ሞልተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን ጸጋ በመግለጽና በላቀ ደረጃ ጥቅም ላይ በማዋል ብልጽግናዋን ለማረጋገጥ የሚተጉ የሌላ ግንባር ጀግኖችንም ፈጥራለች፡፡ የራሱን ወንዝ፣ በራሱ ገንዘብ እና ጥረት በርካታ አሻጥሮችንና መሰናክሎችን ተሻግሮ የሕዳሴ ግድብን ለስኬት ያበቃ ትውልድ ሙሉ ዐርበኛ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን የሚታረስ መሬት ጦም ሳያሳድር፣ ተገቢዉን ግብዓት እና ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ በጋ ከክረምት በማምረት የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጠዉ፤ የእንስሳት ዕርባታ ላይ አተኩሮ በመሥራት፣ የተሻሻሉ ዝርያዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን የሥጋ እና ወተት እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ፍላጎት ለማሟላት የሚተጋዉ አርሶ እና አርብቶ አደር ዐርበኛ ነው፡፡ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ኢንቨስት ያደረገው፣ በኢንቨስትመንቱ በሀገር ውስጥ ያመረተዉን ውጤት ለዜጎች የሚሸጠዉና ለዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ምርቶችን በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኘው ባለሀብት እና ሠራተኛ ዐርበኛ ነው፡፡ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ጸጋዎች፣ የከርሰ ምድር እና የገጸ ምድር ሀብቶች በመለየት ወደ ተጨባጭ ሀብትነት መቀየር ዐርበኝነት ነው፡፡ ከተሞች የሥልጣኔ ማእከል እንደመኾናቸው በመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በጽዱነት ለሌሎች አብነት እንዲኾኑ ማድረግ መቻል ዐርበኝነት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የትናንቷን ዐርበኞች በምትዘክረው ልክ የዛሬና የነገ ዐርበኞቿንም ለመዘከር ቃል ትገባለች፡፡ የአባቶቻችንን የዐርበኝነት መሥዋዕትነት ዋጋ የምንከፍለው የትናንት ድላቸዉን በማስታወስ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ቀና ብለው ቢያዩን “እንኳንም ዋጋ ከፈልን” እንዲሉ ማድረግ ስንችል ነው። ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ የዘመኑን ዐርበኝነት ትግል ማሳካት ይገባናል። የዘመኑ ዐርበኝነት በዋነኝነት ድህነትን ማሸነፍ፣ ራስን መቻል እና የዲጂታል ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ናቸው። የዛሬዋ ኢትዮጵያ የዐርበኝነት ዓውዷ ከትናንቱ በእጅጉ የሰፋ፣ የምልዓተ ሕዝቡን ተሳትፎ በብዙ ግንባሮች የሚጠይቅ ነው፡፡ ልጆቿ ደግሞ ሀገር የጠየቀችውን ኹሉ የመክፈል ልምድ እና ታሪክ አላቸውና በመፍጠንና መፍጠር ያሳኩታል፡፡

የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ/ም