የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ በአርበኞች መታሰቢያ ሐውልት የአበባ ጉንጉን አኖሩ

By ዮሐንስ ደርበው

May 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 84ኛው የአርበኞች የድል በዓል ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በአራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ሐውልት እየተከበረ ነው፡፡

በአከባበሩ ላይም ፕሬዚዳንት ታዬ በአርበኞች መታሰቢያ ሐውልት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮችና አባላት፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአከባበሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡