ስፓርት

አሌክሳንደር አርኖልድ ከልጅነት ክለቡ ጋር እንደሚለያይ አረጋግጧል

By ዮሐንስ ደርበው

May 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከልጅነት ክለቡ ሊቨርፑል ለመልቀቅ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

አሌክሳንደር አርኖልድ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ፤ ራሱን በአዲስ ክለብ እና በተለየ ቦታ ለመፈተሽ በመፈለጉ ከሊቨርፑል ለመልቀቅ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ወደ አዲስ ክለብ መሄዱም ያለውን ሙሉ አቅም አውጥቶ እንዲጠቀም እንደሚያስችለው ነው የገለጸው፡፡

ላሳደገው ክለብም ያለውን ክብር እና ፍቅር ገልጾ፤ ለመልቀቅ የወሰነው ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ጉዳይ አለመሆኑን ጠቅሷል፡፡