የሀገር ውስጥ ዜና

ከእሥራኤል ጋር ትብብራችን በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By ዮሐንስ ደርበው

May 05, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእሥራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ካሉት የእሥራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር ጋር በኢትዮ-እሥራኤል ግንኙነት ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።

ሁለቱ ሀገሮቻችን በታሪክ ሥረ መሠረት ላይ የተገነባ ረዥም ዘመን የቆየ ግንኙነታቸውን ዛሬም ቀጥለዋል በማለት ገልጸው፤ ዛሬ ትብብራችን በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊ፣ በዲፕሎማሲያዊ፣ በማኅበራዊ እና በሌሎችም መስኮች ላይ ተጠናክሮ ቀጥሏል።