የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪውን አቅም በማሳደግ ለነገ መሰረት የሚጥል ነው -ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

By Mikias Ayele

May 06, 2025

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም በማሳደግ ለነገ መሰረት የሚጥል ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።

ፕሬዚዳንቱ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 ከጎበኙ በኋላ በሰጡት ማብራሪያ÷ የኢትዮጵያ ፍላጎት ምርታማነትን በመጨመር ጥቅል ሀገራዊ እድገትን ማሻሻል መሆኑን ተናግረዋል።

በኤክስፖው የቀረቡት ከቆዳ የተሰሩ የተለያዩ ምርቶች በዓለም አቀፍ የጥራት መመዘኛ መስፈርት ደረጃቸውን ያሟሉ መሆናቸውን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ማምረት ከማስቻሉም በላይ የኢትዮጵያን የገበያ መዳረሻ የሚያሰፋ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም በማሳደግ የሥራ እድል የሚፈጥርና ነገ የተሻለ ለማምረት መሰረት የሚጥል መሆኑን ገልጸዋል።

በኤክስፖው የታየው መነቃቃት የኢትዮጵያን የማምረት እቅም እንደሚጨመር ጠቁመው፤ ምርቶቹ ኢትዮጵያ የማምረት  አቅም እንዳላት እና የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ የነገ ተስፋ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በፍቅርተ ከበደ