አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኳታር ንጉስ ግርማዊ ሼኽ ታሚም አል ታኒ የተላከላቸውን መልዕክት መቀበላቸውን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኳታር ንጉስ ግርማዊ ሼኽ ታሚም አል ታኒ የተላከ መልዕክት መቀበላቸውን ጠቅሰዋል፡፡
መልዕክቱን ይዘው ከመጡት የኳታር ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን አብዱልአዚዝ አል ካሊፊ (ዶ/ር) ጋርም መወያየታቸውን ነው ያስታወቁት፡፡