አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የሐዋሳ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ታፈሰ ሰለሞን በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሐዋሳ ከተማ ወደ ድል ሲመለስ ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ሐዋሳ ከተማ በ31 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ድሬዳዋ ከተማ በ29 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ቀን 10 ሠዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡