አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማህበረሰብ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።
“ሰብዓዊነትን እናጽና” በሚል መሪ ሀሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ78ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ67ኛ ጊዜ የዓለም ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ቀን እየታሰበ ነው።
ዕለቱን አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለሚያከናውናቸው ተግባራት አስተዋጽኦ እያበረከቱ ለሚገኙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በመልዕክታቸውም ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማህበረሰብ፣ አጋር አካላት፣ አባላት፣ በጎ ፈቃደኞች እና ሰራተኞች ልባዊ ምስጋናቸውን እንዳቀረቡ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዳማ ከተማ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ሥራ አስፈፃሚዎች፣ ሠራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞችና የአጋር አካላት ተወካዮችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቧል።