የሀገር ውስጥ ዜና

በመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይዎት አለፈ

By Yonas Getnet

May 08, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ በላሊበላ ከተማ ደብረ ዘይት ቀበሌ ሽምብርማ አካባቢ ቁጥር 2 በተባለ ስፍራ በደረሰ የመኪና መገልበጥ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይዎት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በ5 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የላሊበላ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ሳጅን ሃብትየ ካሳው ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

አክለውም አደጋው የደረሰው ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው ብለዋል።

በዮሐንስ ደርበው