አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚቀጥለው ሳምንት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ህፃናት የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት እንደሚሰጥ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ም/ኃላፊ ናፍቆት ብርሃኑ፥ ክትባቱ በጊዜያዊና በቋሚነት በተዘጋጁ ህክምና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ገልጸው፥ ለዘመቻው ስኬታማነት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የክትባት ዘመቻው ከግንቦት 6 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ በቢሮው የእናቶችና ህፃናት ስርዓት ምግብ ዳይሬክቶሬት የህፃናትና ክትባት አስተባባሪ አቶ አብዱልቃድር ሁሴን ገልጸዋል፡፡
ክትባቱ ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 59 ወር ላሉ ህፃናት በክልሉ ሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በማቴዎስ ፈለቀ