አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈው ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ የተሰማውን ሃዘን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ባልደረባ የነበሩት ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያለ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተይዘው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡