አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕንድ እና ፓኪስታን በአሜሪካ አሸማጋይነት አስቸኳይ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መረጃ፤ ሁለቱ ሀገራት አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ በአሜሪካ አሸማጋይነት ረዘም ያለ ሠዓት መውሰዱን ጠቅሰዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች ጥብብ የተሞላበት ስምምነት ላይ በመድረሳቸውም ትራምፕ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡
የፓኪስታን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሻቅ ዳር በበኩላቸው፤ አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነቱን መቀበላቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ሀገራቸው አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነቱን መቀበሏን ያረጋገጡት የሕንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪክራም ሚስሪ፤ የፊታችን ሰኞ ፊት ለፊት በመገናኘት ንግግር ለማድረግ ቀን ቆርጠናል ብለዋል፡፡
ባለፈው ወር በፓኪስታን ጉብኝት ሲያደርጉ በነበሩ የሕንድ ዜጎች ላይ በታጣቂዎች ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ፤ ሁለቱ ሀገራት ወደለየለት ግጭት መግባታቸው ይታወቃል፡፡
በአቤል ንዋይ