የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የአፍሪካ ከፍተኛውን የስፖርት ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

By Tibebu Kebede

August 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የአፍሪካ ብሄራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር /አኖካ/ ለኦሎምፒክ ስፖርት ዕድገት ድጋፍ ላደረጉ መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።

ለኢትዮጵያ ስፖርት እና ለኦሎምፒክ ንቅናቄ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ይህ በአፍሪካ በስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የሆነው ሽልማት ተሸላሚ መሆናቸውን አኖካ አስታውቋል።