አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጣሊያናዊው ካርሎ አንቼሎቲ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸው ይፋ ሆኗል፡፡
ሪያል ማድሪድ ከሪያል ሶሴዳድ የሚያደርገው የላሊጋው ጨዋታም በማድሪድ ቤት የመጨረሻ ኃላፊነታቸው እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
አንቼሎቲ በፈረንጆቹ ግንቦት 26 በይፋ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸውን እንደሚረከቡ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
የ65 ዓመቱ አሰልጣኝ አንቼሎቲ፤ በብራዚል ታሪክ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር አሰልጣኝ መሆናቸውን ዘገባው አመላክቷል፡፡
በአቤል ንዋይ