ስፓርት

አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በባርሴሎና ለመቆየት ተስማሙ

By Mikias Ayele

May 12, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆያቸውን ውል ለመፈረም ከክለቡ ጋር ተስማምተዋል፡፡

ከትናንት ምሽቱ የኤል ክላሲኮ ድል በኋላ ዩዋን ላፖርታን ጨምሮ የክለቡ አመራሮች ከአሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ እና ወኪላቸው ጋር መወያየታቸውን ባርካ ዩኒቨርሳል ምጮቹን ጠቅሶ  ዘግቧል፡፡

ከውይይቱ በኋላም ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ እስከ ፈረንጆቹ 2027 ድረስ በካታሎኑ ክለብ የሚያቆያቸውን ውል ለመፈረም ከክለቡ አመራሮች ጋር መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

አሰልጣኙ ባርሴሎናን በሻምፒየንስ ሊጉ ለግማሽ ፍጻፃሜ ሲያደረሱ፤ በላሊጋውም የደረጃ ሰንጠረዡን በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡