አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የኮንፈረንስ ቱሪዝም የስበት ማዕከል እየሆነች ነው ሲሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በዘርፉ የፖሊሲ ለውጥ መደረጉን ጨምሮ ኮሪደር ልማትና ሌሎች ምቹ መሠረተ-ልማቶች፣ ከቪዛ ጋር ተያይዞ የተደረጉ ማሻሻያዎች ኢትዮጵያን ተመራጭ እንድትሆን አስችለዋታል ብለዋል፡፡
የከተማ ቱሪዝም ኢኮኖሚውን በከተማ ደረጃ ለማነቃቃት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያን ባህሎች፣ የዕደ ጥበብ ውጤቶች እና ሌሎች ምርቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ የቱሪዝም ኮንፈረንስ ዕድል እንደሚፈጥር አመላክተዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን