አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮሪደር ልማቱ የአደጋ ስጋትን በመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አሕመድ መሐመድ ገለጹ፡፡
ከዚህ ቀደም ውስብስብ በሆኑ የኤሌክትሪክ ገመዶች ሳቢያ አደጋዎች ሲከሰቱ ለመቆጣጠር አዳጋች እንደነበር አስታውሰዋል።
አሁን ከኮሪደር ልማቱ ጋር ተያይዞ የተገነቡ መሠረተ ልማቶች የኤሌክትሪክ ገመዶች ከመሬት ስር እንዲቀበሩ እና የእሳት ማጥፊያ ውኃም በግማሽ ኪሎ ሜትር ልዩነት መሠራቱን ጠቅሰዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር) እንዳሉት፤ እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማቶች አደጋን የመቀነስና መቋቋም አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡፡
በመቅደስ የኔሁን