ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካ ከሶርያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ እንደምትፈልግ ገለጸች

By Hailemaryam Tegegn

May 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ በሶርያ ላይ ተጥሎ የቆየውን ማዕቀብ እንደምታነሳና ግንኙነቷን ለማደስ እንደምትፈልግ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስታወቁ፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ፕሬዚዳንቱ፤ ከሶርያ ፕሬዚዳንት አሕመድ አልሻራ ጋር በሳዑዲ ዓረቢያ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሀገራቸው ከሶርያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ የሚቻልባቸውን አማራጮች እያማተረች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሁለቱ መሪዎች ውይይት ፕሬዚዳንት አሕመድ አልሻራ መንግሥታቸውን ለማጠናከር እያደረጉ ላሉት ጥረት መልካም አጋጣሚ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም ሶርያ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት እንድታሻሽል ትራምፕ ማሳሰባቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

የትራምፕ እና አሕመድ አልሻራ ውይይት ከፈረንጆቹ 2000 ወዲህ በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል የተደረገ የመጀመሪያው ውይይት መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሀገራቸው በሶርያ ላይ ተጥሎ የቆየው ማዕቀብ እንደሚነሳ ከገለጹ በኋላ፤ ሶርያውያን ወደ ዐደባባይ በመውጣት ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ