ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል እና ስሑል ሽረ ነጥብ ተጋሩ

By ዮሐንስ ደርበው

May 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተገናኙት መቻል እና ስሑል ሽረ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

12 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የመቻልን ግብ ሽመልስ በቀለ ሲያስቆጥር፤ የስሑል ሽረን ደግሞ ኤልያስ አሕመድ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

ቀደም ብሎ በተካሄደ የዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባሕርዳር ከተማ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡