የሀገር ውስጥ ዜና

በወላይታ ሶዶ ከተማ በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Yonas Getnet

May 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው ከሃዋሳ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ የሚጠራ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡

በተከሰተው አደጋም የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ አስተዳደር ዋና ሳጅን ዝናቡ ገዛኸኝ ተናግረዋል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች አቅራቢያ በሚገኙ ጤና ተቋማት ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑን ዋና ሳጅን ዝናቡ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡

በማስተዋል አሰፋ