ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ውይይት በኢስታንቡል መካሄድ ጀመረ

By Mikias Ayele

May 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ እና ዩክሬን ተደራዳሪ ልዑካን ቡድን አባላት በቱርክ ኢስታንቡል እየተወያዩ ነው፡፡

በአሜሪካና ቱርክ አደራዳሪነት እየተካሄደ የሚገኘው የሀገራቱ የሰላም ውይይት ከሶስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ የገጽ ለገጽ ምክክር ነው ተብሏል፡፡

የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚስትር ሃካን ፊዳን ÷ ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ሰላም ስምምነት ለመምጣት ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት ማድረግ አለባቸው ያሉት ሚነስትሩ÷ ውይይቱ ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አስከፊ የተባለውን ጦርነት ለማስቆም ወሳኝ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ ዩክሬን ወደ ሰላም ስምምነት ለመምጣት ሩሲያ ለ30 ቀናት የሚቆይ ተኩስ አቁም እንድታደርግና ሁሉንም የጦር ምርኮኞች እንድትፈታ መጠየቋ ተሰምቷል፡፡

ሩሲያ በበኩሏ ዩክሬን የጠየቀችውን የተኩስ አቁም ለማድረግ እና ወደ ሰላም ድርድር ለመምጣት ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻለች፡፡

ይሁን እንጂ የተኩስ አቁሙን ዩክሬን ወታደሯን ለማደራጀትና የጦር መሳሪያ ለማሰባሰብ ልትጠቀምበት ትችላለች የሚል ስጋት እንዳላት ነው አጽንኦት የሰጠችው፡፡

በውይይቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና በአሜሪካ የዩክሬን እና ሩሲያ ልዩ መልዕክተኞች መሳተፋቸውን ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ