አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ራምኬል ጀምስ እና አማኑኤል አድማሱ አስቆጥረዋል፡፡
የዛሬው የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ÷ ምሽት 12 ሰዓት ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ሊጉን ኢትዮጵያ መድን በ60 ነጥብ ሲመራ÷ ኢትዮጵያ ቡና በ51 ነጥብ ይከተላል፡፡
ወራጅ ቀጣና ላይ መቐለ 70 እንደርታ፣ አዳማ ከተማ፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተቀምጠዋል፡፡