የሀገር ውስጥ ዜና

በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚሠሩ ሥራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን አለባቸው

By ዮሐንስ ደርበው

May 24, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው በፈረንሳይ ፓሪስ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በማብራሪያቸውም፤ በፈረንሳይ ጉብኝታቸው ወቅት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በርካታ ችግር ፈቺ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሥራዎች መሠራታቸውን መመልከታቸውን አንስተዋል፡፡

ከጉብኝታቸው ግብዓት ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ በስታርት አፕ ላይ በትኩረት መሥራት እንዳለብን  ተረድተናል፤ ወጣቶች ሐሳብ ይዘው ሲመጡ ለሀገር እንዲጠቅም ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የተሠሩ ውጤታማ ሥራዎችን ዐይተናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያም በቴክኖሎጂው ዘርፍ የጀመረቻቸውን ሥራዎች አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል፡፡

በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሥራዎችን በምርምር እና በጥናት አስደግፎ መሥራት ከተቻለ፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተለያዩ ሀገራት ጋር እንዴት መወዳደር እንደምትችል ትምህርት ወስደናል ነው ያሉት፡፡

ሀገራት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ያመጧቸውን ውጤቶች መመልከታችን፤ እኛም በቴክኖሎጂው ዘርፍ በይበልጥ በትኩረት እንድንሠራ ያግዘናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ