ስፓርት

የ2024/25 እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናቀቀ

By Mikias Ayele

May 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2024/25 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረጉ መርሐ ግብሮች ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡

ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ፣ ቼልሲ፣ አርሰናል እና ማንቼስተር ዩናይትድ ሲያሸንፉ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ ጋር አቻ ተለያይቷል።

ውጤቱን ተከትሎም ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል በ84 ነጥብ ሲያጠናቅቅ፤ አርሰናል በ74 ነጥብ ሁለተኛ፣ ማንቼሰተር ሲቲ በ71 ነጥብ ሶስተኛ እንዲሁም ቼልሲ በ69 ነጥብ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡

ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ፉክክር ኒውካስል፣ ኖቲንግሃም ፎረስት እና አስቶንቪላ በመሸነፋቸው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ሳይታሰብ የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

18 የፕሪሚየር ሊግ ሽንፈት ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 42 ነጥቦችን በመሰብሰብ 15ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡