ስፓርት

ሊቨርፑል ድሉን ከደጋፊዎቹ ጋር እያከበረ ነው

By Adimasu Aragawu

May 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2024/25 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ድሉን ከደጋፊዎቹ ጋር እያከበረ ይገኛል።

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በአንፊልድ ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር ከደጋፊዎቹ ጋር 20ኛ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ድሉን እያከበረ ነው፡፡

በኮቪድ 19 ምክንያት ከአምስት ዓመት በፊት ሻምፒዮን ሆኖ ድሉን ከደጋፊው ጋር ማክበር ያልቻለው ክለቡ÷ 20ኛውን የሊግ ዋንጫ አሳክቷል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ትናንት ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን÷ ሊቨርፑል በውድድር ዓመቱ በሊጉ ባደረጋቸው 38 ጨዋታዎች 84 ነጥብ በመሰብሰብ በአንደኝነት ማጠናቀቁ አይዘነጋም፡፡