የሀገር ውስጥ ዜና

የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ምሰሶዎችን ለማሳደግ የሰው ሠራሽ አስተውሎትን አጠቃቀም ማጎልበት ይገባል

By ዮሐንስ ደርበው

May 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ማዋል የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ምሰሶ ዘርፎችን ዕድገት በማፋጠን ረገድ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ምሁራን ገለጹ፡፡

የምጣኔ ሃብት ተመራማሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) አንዳሉት፤ ሰው ሠራሽ አስተውሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ የገበያ ተወዳዳሪነታችንን እንድናሳድግ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያም ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታውን በቶሎ እንድትቀላቀል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት፡፡

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኤአይ ተመራማሪ ሰዒድ ኢሳ በበኩላቸው፤ ዲጂታል ሰው ሠራሽ አስተውሎትን መሠረት ያደረጉ ሥራዎች መሠራታቸው በቴክኖሎጂ የታገዙ አሠራሮች እና ስታርትአፕ ቢዝነሶችን ለመጀመር እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በኢትዮጵያ የተጀመረው የ5 ሚሊየን ኮደሮች ስልጠና መጠናከር እንዳለበት የመከሩት ምሁራኑ፤ የተለያዩ ሀገራት በዚህ ስልጠና ተጠቅመው ስኬታማ መሆን መቻላቻውን ጠቅሰዋል፡፡

ጸጋዬ ንጉስ