አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በአቻ ውጤት ተለያተዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተደረገው ጨዋታ ግብ አልተቆጠረበትም።
ቀደም ሲል ዛሬ ረፋድ 3:30 ላይ በተካሄደ ጨዋታ አዳማ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን በረከት ወ/ዮሐንስ (በራስ ላይ) ባስቆጠራት ግብ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።
የ32ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ምሽት 12 ሰዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ ወላይታ ድቻ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ይገናኛሉ።