ስፓርት

ሪያል ማድሪድ አሌክሳንደር አርኖልድን አስፈረመ

By ዮሐንስ ደርበው

May 30, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ኃያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

አሌክሳንደር አርኖልድ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከልጅነት ክለቡ ሊቨርፑል ለመልቀቅ መወሰኑን ከሣምንታት በፊት ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

በወቅቱም፤ ራሱን በአዲስ ክለብ እና በተለየ ቦታ ለመፈተሽ በመፈለጉ ከሊቨርፑል ለመልቀቅ መወሰኑን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡

ወደ አዲስ ክለብ መሄዱም ያለውን ሙሉ አቅም አውጥቶ እንዲጠቀም እንደሚያስችለው መግለጹ ይታወቃል፡፡