የሀገር ውስጥ ዜና

በሀገራዊ ምክክሩ የ2ኛው ቀን የፌዴራል ተቋማትና ማኅበራት አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ እየተካሄደ ነው

By Adimasu Aragawu

May 31, 2025

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገራዊ ምክክሩ የፌዴራል ተቋማትና ማኅበራት አጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።

በሰባት ቡድኖች ተካፋፍለው ትናንት በአጀንዳ ሐሳቦቻቸው ላይ ሲመክሩ የነበሩት ተወያዮቹ÷ ዛሬ በቡድኑ አባሎቻቸው የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን እያጠናቀሩ ነው።

በዚህም የንዑስ ቡድን አጀንዳዎች ከተጠናቀሩ በኋላ በየቡድን ጸሐፊዎች እና ሰብሳቢዎች አማካይነት ለተሳታፊዎች በንባብ ቀርቧል።

በመጨረሻም የንዑስ ቡድን ጠቅላላ አጀንዳዎች ተሰብስበው የሰባት ቡድን አጀንዳዎች የሚደራጁ ይሆናል።

በአጀንዳ ማሰባሰቡ ላይ ማኅበራትና ተቋማት፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪና የማኅበረሰብ አንቂዎቸ፣ የዴሞክራሲ እና የሃይማኖት ተቋማት፣ የጸጥታና ደኅንነት አካላት፣ የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም የመንግሥት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በይስማው አደራው