የሀገር ውስጥ ዜና

የቻይና ቀዳማዊት እመቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረጉ

By Feven Bishaw

August 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ቀዳማዊት እመቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያግዙ ቁሳቁሶችን አበረከቱ።

ቀዳማዊት እመቤት ፒንግ ሊዋን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር ቁሳቁሶችን ማበርከታቸውንም የኢትዮጵያ ቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ባወጣው መረጃ አስታውቋል።