👉 ኢትዮጵያዊነት የጋራ ዕጣ ፋንታ ነው።
👉 የሚያሰባስበን እና እንደቤተሰብ እንድንታይ የሚያደርገን ትርክት ያስፈልጋል።
👉 ብሔራዊ ጥቅም ማለት በትውልድ ቅብብሎሽ መካከል የሚጸናና ኢትዮጵያዊነትን የሚያቆይ ሥራ ነው።
👉 ብሔራዊ ጥቅም ስንል ከእኛ ከግል ፍላጎት እና መሻት የተሻገረ ማለት ነው።
👉 በአንድ ትውልድ፣ በአንድ ቤተሰብ፣ በአንድ ቡድን ሀገር ተሠርቶ አያልቅም፤ ሀገር የቅብብሎሽ ውጤት ነው።
👉 ኢትዮጵያዊነት ሲመቸን፣ ሲደላን፣ ጥቅም ስናገኝበት የምናዜመው የምናወድሰው ሲከፋን ሳይመቸን ሲቀር ህልሞቻችን ሲጨነጋገፉ የምንተወው የወረት ጉዳይ አይደለም።
👉 ኢትዮጵያዊነት ኩልል ብሎ የሚፈስ ጅረት ነው። አንዳንዴ ዘንቦ ሊደፈርስ ይችላል ነገር ግን ሰክኖ ይጠራል።
በዮናስ ጌትነት